የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302

ፍሬድማን ሩቢን የህግ ቢሮ

ሲያትል፡ አሜሪካ።

ማርች 13 ቀን፣ 2019 ዓ.ም

ፍሬድማን ሩቢን የህግ መስሪያ ቤት፤ ቦይንግ 737 Max ከተሰራበት ኤቨርት ከተማ፣ ዋሺንግተን ክፍለ ግዛት – በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል። ከዚህ በፊት በኢንዶኔዥያ ለደረሰው የቦይንግ 737 Max፤ የጉዳት ሰለባዎች የህግ ጠበቃ ሆነን ሰርተናል። እስካሁን ለደረሰው የአውሮፕላን አደጋ፤ አንደኛው መንስኤ የቦይንግ ስራ ጉድለት ነው። እኛ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች አስፈላጊው የጉዳት ካሳ እንዲከፈላቸው እናስደርጋለን።

በርግጥ ምን እንደተፈጠረ እውነቱን መፈለግ ያስፈልጋል?

ሁሉም የአውሮፕላን አደጋዎች ከደረሱ በኋላ፤ ምንግዜም ቢሆን ምርመራ ይደረጋል። በአንዛኛው ግን ይህ ምርመራ የሚካሄደው በአየር መንገዱና በአውሮፕላን ፋብሪካው ተወካዮች፤ ወይም የሁለትዮሽ ስምምነት ነው። ይህን ሁኔታ… አንዳንዶች “የዶሮ ቤትን ለመጠበቅ ቀበሮን ዘበኛ ማድረግ እንደማለት ነው።” ይላሉ። ብዙውን ግዜ አደጋው የደረሰባቸው ቤተሰቦች፤ በምርመራው ሂደት ላይ ተሳታፊ አይሆኑም። የአቪዬሽን ጠበቃ በመቅጠርና ህጋዊ ውል በመፈጸም ማንኛውም ቤተሰብ የምርመራውን ውጤት በቅርብ የማወቅ እድል ያገኛሉ። ህጋዊ ውክልና ካገኘን ደግሞ፤ አስፈላጊ የሆኑ ጥያቄዎችን እናቀርባለን። በጥያቄያችንም መሰረት…አየር መንገዱም ሆነ የቦይንግ ካምፓኒ መልስ የመስጠት ግዴታ ይኖርባቸዋል። ይህ ብቻም አይደለም። የራሳችንን የምርመራ ልዑካን ቡድን አባላት፤ የአውሮፕላኑ አደጋ የደረሰበት ቦታ ድረስ እንልካለን። በፍንዳታው የደረሰውን አደጋ እና የጥገና መዝገቡን እናጠናለን፤ እናም ከፍንዳታው በስተጀርባ ምን እንደተፈጠረ እውነትን እንፈልጋለን።

ይህ በሌላ ቤተሰብ ላይ፤ በጭራሽ ሊደርስ የማይገባው ነው!

በዚህ አመት በቦይንግ 737 ማክስ ላይ ተመሳሳት ሲደርስ፤ ይህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ላይ የደረሰው አደጋ ሁለተኛው መሆኑ ነው። የመጀመሪያው አደጋ በ Lion Air ላይ ሲደርስ፤ የችግሩ መንስኤ የቦይንግ 737 ማክስ መሆኑን አየር መንገዱ ገና አላወቀም ነበር። የአውሮፕላኑን የበረራ ፍሰት ለመቆጣጠር የሚያግዘው የበረራ ሰነድ (flight manual) ሊኖራቸው እንደሚገባ ለLion አየር መንገድ ስላልተነገራቸው፤ ተመሳሳይ የሆነው አደጋ በኢንዶኔዥያ ደረሰ። ሆኖም በ Lion አየር መንገድ ላይ አደጋው ከደረሰ በኋላ፤ ለሁሉም አየር መንገዶች የበረራ ማኑዋል መስጠት እንዳለበት የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር ትዕዛዝ ሰጥቶታል። በ Lion አየር መንገድ ላይ አደጋ ከደረሰ በኋላ፤ ይህ አዲስ የበረራ ማኑዋል ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ተሰጥቶ ሊሆን ይችል ይሆናል። ይህ ብቻ ግን በቂ አይደለም። ከዚህ አደጋ በኋላ፤ ተመሳሳይ የሆነ አደጋ እንዳይደርስ እና ለውጥ መደረጉን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። 

ይህ አይነቱ አደጋ እንዳይደገም ወይም በሌላ ቤተሰብ ላይ እንዳይደርስ መሆን አለበት።

ሃላፊነትን መውሰድ

ማንኛውም በረራ ምቹ መሆኑ ቀርቶ አደጋ ካጋጠመው አየር መንገዱ፤ ወይም የአውሮፕላኑ ማምረቻ ካምፓኒ በጋራ ወይም በተናጠል ሃላፊነት ሊወስዱ ይገባቸዋል። አንዳንድ ግዜ አየር መንገዶች ወይም የአውሮፕላን አምራቾች የነሱን ጥፋት በሌላ ሰው ላይ ማላከክ ይፈልጋሉ። እውነቱን በማጋለጥ ይህን እናስቆማለን። ይህ አይነቱን ምግባር የምናስቆመው፤ አየር መንገዱ ወይም የአውሮፕላን አምራቹ ለፈጸሙት ጉዳት እና ለጠፋው ህይወት፤ ለቤተሰቦች አስፈላጊውን የካሳ ክፍያ እንዲፈጽሙ በማድረግ ነው። ከዚያ በኋላ በርካሽ እና በአቋራጭ መንገድ ማምለጥ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። አየር መንገዱ ወይም አውሮፕላን አምራቹ ሃላፊነት የማይወስዱ ከሆነ ግን፤ በህግ ሃላፊነት እንዲወስዱ እናደርጋቸዋለን።

በዚህ አጋጣሚ ቤተሰብዎን በዚህ አደጋ አጥተው ከሆነ፤ ልባዊ ሃዘናችንን እንገልጻለን። You may also Contact Law Offices of Shakespear N. Feyissa associating with Friedman Rubin at (206) 292-1246 (Office) or (206) 380-9309 (Mobile).